ሙያዊ የሆነ የትርጉም አገልግሎት በኢትዮጵያ

አጋራችን በመሆን የምንሰጣቸው የተለያዩ እውነተኛ የዋጋ ቅናሾች ይጠቀሙባቸው

እየተሠራልዎት ያለውን ትርጒም ሥራ ሂደት ደረጃ መከታተል ይችላሉ፣ ለትላልቅ ፕሮጄክቶች በየቀኑ ሪፖርት ያገኛሉ

ዋጋችን ከ 0.05 ዶላር (5.50 ብር) እስከ 0.25 ዶላር (12.63 ብር) ክልል ውስጥ ነው

ላልረኩበት ሥራ ያለ ቅድመ ሁኔታ ገንዘብዎ ተመላሽ ይሆናል፤ ቀነ ቀጠሮ ሳይከበር ሲቀር እና የፊደል ግደፈት ሲገኝ ከክፍያው ላይ ተቀናሽ ይሆናል

ፋይልዎን ያስገቡ፦የትርጉም ሥራዎን በይነ መረብ ተጠቅመው ያግኙ

ከውድ ደንበኞቻችን እና አጋሮቻችን መካከል ጥቂቶቹ

የኢትዮጵያ እና ምሥራቅ አፍሪካ ቋንቋዎች የሎካላይዜሽን እና የትርጉም አገልግሎት

እንኳን ደኅና መጡ!                                  
ከትርጉም አገልግሎት ጋር በተያያዘ አስቸጋሪ ሁኔታ ገጥሞዎት ያውቃል? ጠንቃቃ የሆኑ ሙያዊ ተርጓሚዎችን የያዘ እና እምነትዎን ሊጥሉበት የሚችሉ የትርጉም አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት ይፈልጋሉ? ለዘገዩ ሥራዎች የሚሰጡ ሰበቦች ሰልችትዎታል? ጥራታቸውን ባልጠበቁ የፕሩፍሪዲንግ እና ቅርጸት የማስተካከል ሥራዎች ምክንያት ተበሳጭተዋል? ትርጉሙ ተሠርቶ የሚረከቡበት የጊዜ ገደብ ወጪ ከሚያደርጉት ገንዘብ ጋር አይመጣጠንም ብለው ያስባሉ? የመኪና ማቆሚያ ችግር ገጥምዎታል? ተርጓሚዎች ወይም የትርጉም ኤጀንሲዎች የእርሶን መሥፈርቶች ባለመረዳታቸው ቅሬታ አድሮብዎት ያውቃል?

ስለሚፈልጉት የትርጉም እና የሎካላይዜሽን አገልግሎት ሌሎች በርካታ ችግሮች እና ስጋቶች ሊኖሩዎት ይችላል። እኛ ጋር ሁሉም ቅሬታዎችዎ ተረጋግጠው ተቀባይነት የሚያገኙ ይሆናል። ደንበኞቻችን ከዚህ በፊት በነበሯቸው አወንታዊ ያልሆኑ ገጠመኞች ምክንያት የሚኖሯቸውን ቅሬታዎች በጥንቃቄ በማጥናት በቴክኖሎጂ የተደገፉ የተሻሉ መፍትሔዎችን አዘጋጅተናል። ከእርስዎ ጋር ለረጅም ጊዜ ዘላቂ የሚሆን የሥራ ግንኙነት እና አጋርነት ለመገንባት እንፈልጋለን። የትርጉም ሂደታችንን ጨምሮ ሌሎች ተጨማሪ ዝርዝሮችን ለማግኘት ያነጋግሩን።

አጋሮቻችን

ተመጣጣኝ የሆነ የዋጋ ተመን

  • ግልጽ የሆነ በቃል የሚሰላ የዋጋ ተመን
  • ለግለሰቦች፣ የአገር ውስጥ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ኩባንያዎች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የተለያዩ ፓኬጆች

ቅልጥፍና

ከ 50 በላይ በሆኑ በሙያው ብቃታቸው የተረጋገጠ እና በሁሉም ዋና ዋና የሰዓት ቀጠናዎች በሚሠሩ ተርጓሚዎቻችን በመጠቀም የትርጉም ፍላጎትዎ ስፋት ምንም ያህል ቢሆን በሚፈልጉት ፍጥነት ሠርተን እናስረክብዎታለን።

የትርጉም ጥራት እና ወጥነት

የተቀናጀው Application Programming Interface ( API) እና በውስጥ የተካተቱት የጥራት መሣሪያዎች የሥራ ፍሰት ዝግመትን በማስወገድ በሁሉም ፕሮጀክቶች ውስጥ ወጥነትን እና ጥራትን ያረጋግጣሉ።

አገልግሎቶቻችን

ሎካላይዜሽን

ሎካላይዜሽን አንድን ምርት ወይም አገልግሎት ከአንድ አካባቢ ባህልና ወግ ጋር በሚጣጣም መልኩ አዋህዶ የማቅረብ ሂደት ነው በማለት ሊበየን ይችላል። የሎካላይዜሽን ዓላማ በአንድ ዒላማ በተደረገ ገበያ ውስጥ ምርቱ ወይም አገልግሎቱ በራሱ በገበያው ውስጥ ባሉ ታዳሚዎች ባህልና ወግ ተቃኝቶ በአገሬው ዜጎች እንደተመረተ መስሎ አገልግሎቱ ወይም ምርቱ እንዲቀርብ ማድረግ ነው።

የትርጉም አገልግሎት

ትርጒም ሥራ በአንድ ቋንቋ የተሰጠ አንደምታን ለዛና ስሜቱን ሳያጣ ወደ ሌላ ቋንቋ እንዳለ የማስተላለፍአእምሮን የሚጠቀም ሥራ ነው። በአንድ ቋንቋ ያሉትን አለባውያን በሌላ ቋንቋ ወደ ያሉት አቻ ፍቺዎች የማስተላለፍ ተግባር ነው። ትርጒም ሥራ የአንድ ጽሑፍ ይዘት ከምንጭ ቋንቋ ወደ ዒላማ ቋንቋ የሚተላለፍበት ሥራ ነው (Foster, 1958)።

ተጨማሪ አገልግሎቶች

ኢትዮስታር ለፍላጎትዎ ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን ይሰጣል፣ የሚተረጎሙ ወይም የሚተረጎሙ ሰነዶች የግል፣ የንግድ ወይም የድርጅት ሊሆኑ ይችላሉ። ስለአገልግሎቶቻችን የበለጠ ይወቁ።

ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን: